ዛሬም አለሁ
ግጥምና ዜማ - ኢየሩሳሌም ነጊያ
ሙዚቃ ቅንብር - ዳዊት ለሚ
ሚክሲንግና ማስተሪንግ - ንጹሕ ይልማ
ሞሽን ግራፊክስ - ቲራጎ ታደሰ
/ @eyitagraphicsmotion
#Addis_Ababa #Eyerusalem_Negiya #Volume_3
ዛሬም አለሁ
አብዝቼ ጨምሬ ስምህን ልባርከው
ኢየሱስ አንተ ነህ ነፍሴን የወደድከው
አብዝቼ በብዙ ስምህን ልባርከው
ኢየሱስ አንተ ነህ ነፍሴን የወደድከው
እስኪ ጨማምሬ ስምህን ልባርከው
ያደረግክልኝን ምህረት እያየው
እስኪ ጨማምሬ ስምህን ላድንቀው
የሰራህልኝን በጎነት እያየሁ
እየወድከኝ ዛሬም አለሁ
እየራራህልኝ ዛሬም አለሁ
ይቅር እያልከኝ ዛሬም አለሁ
ህይወት ሆነኸኝ ዛሬም አለሁ
እንደገና(*2) እንደገና በፍቅርህ አቀረብከኝ
እንደገና ልጅ አረከኝ
እንደገና(*2) እንደገና በምህረትህ አዘንክልኝ
እንደገና ያንተ አረከኝ
ያወቅኩት እውነት የተረዳሁት
ምህረትህ ገኖ እንዳለሁ በህይወት
የሚገባኝ ይሄ ነው በየዕለት
ፍቅርህ አልራጠም
ምህረትህ አልነጠፈም
የትናንት መውደድህ ለብ እንኳን አላለም
እየወደድከኝ ዛሬም አለሁ
እየረዳኸኝ ዛሬም አለሁ
እያፅናናኸኝ ዛሬም አለሁ
እያፀናኸኝ ዛሬም አለሁ
ክብር ይሁን ለዘልአለም
ምስጋና ላንተ ለዘልአለም
ቸር አምላክ ነህ እና ለዘልአለም
የሚመስልህ የለም ለዘልአለም
ለዘልአለም እንዳንተ ያለ የለም
ለዘልአለም የሚመስልህ የለም
ለዘልአለም እንዳንተ ያለ የለም
ለዘልአለም የሚመስልህ የለም
●Subscribe 👇
/ @eyerusalemnegiyaofficialch5641