የማያወላዳ(YEMAYAWELADA ) ኢየሩሳሌም ነጊያ Eyerusalem Negiya (Jerri )Official

Published: 01 January 1970
on channel: Eyerusalem (Jerri)Negiya Official channel
100,832
like

በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ። 2ጢሞ 3:12

1 ዛሬን ትቶ እሩቅ ለነገ ነዋሪ
ጎዳናው ጠባብ ነው እግዚአብሔር ፈሪ
ጥቂቱን እንጀራ አመስግኖ የበላ
ስለ ሀቅ የኖረ ሆነ የተጠላ
ከእውነት ጋር የሚኖር ሁሌ የሚሰደድ
መቼ ተወዳጅ ነው በብዙሐኑ ዘንድ
ስለጽድቅ ኖሮ
ከእውነት ጋር አብሮ
ይሻላል መሰደድ
ትቶ የሀጥን መንገድ

አዝ - ከባድ ነው መንገዱ
ታምነው ለሚሄዱ
ወለም ዘለም ሳይሉ መስቀሉን ከያዙ
ዋጋ ያስከፍላል ከእውነት ጋር ሲጘዙ
መቼ የዋዛ ነው በዝቶበት ጥምዝምዝ
ፍፃሜው ግን ያምራል የለበትም መዘዝ

2 ሸንጋይ መልዐክ መስሎ በቃሉ ሲነግድ
በምስባኩ ቆሞ በድፍረት ሲጛደድ
ያላለውን ብሎ በሐሰት መሸቀጥ
እውነትን ማድበስበሰ ሀጢአት ሀቅን መርገጥ
ሺ አመት ላይኖር ህሊናን መሸጡ
ፀፀቱ ለራስ ነው ዋላ ሲጋለጡ
ስለጽድቅ ኖሮ
ጌታን አስከብሮ
ይሻላል መሰደድ
ትቶ የሀጥን መንገድ

አዝ - ከባድ ነው መንገዱ
ታምነው ለሚሄዱ
ወለም ዘለም ሳይሉ መስቀሉን ከያዙ
ዋጋ ያስከፍላል ከእውነት ጋር ሲጘዙ
መቼ የዋዛ ነው በዝቶበት ጥምዝምዝ
ፍፃሜው ግን ያምራል የለበትም መዘዝ

3 አስመስሎም መኖር ዋሽቶም አጭበርብሮ
ለጥቂት ቢያኖርም ላይን አሳምሮ
ምንደኛው ጘዳውን ማጀቱን ሊሞላ
ይሉኝታ መች ያውቃል ምስኪኑን ሲያጉላላ
አንድ ሆድን ለመሙላት ደሀውን ቀምቶ
ጡር መሰብሰብ ምን ነው ፍርድ እንዳለ እረስቶ
የቀናው ይመስላል ያገኘ እፎይታ
የሄደው ሲመለስ የለም በዚያ ቦታ

አዝ- ቀላል ነው መንገዱ
ቧቋራጭ ሲሄዱ
እዛም እዚህም ካሉ እንዲያው ሲፋንኑ
ልፋት አይጠይቅም ለሀሰት ከወገኑ
ልጘም የለበትም ሰፊነው መንገዱ
ፍፃሜው ያስፈራል መዘዙ ነው ጉዱ

-መወልሸሻ የለው የማያውላዳ
ጘዳናው አንድ ነው ቢበዛውም ፍዳ
እስከመጨረሻው ሊጛዙ ለወደዱ
ንፁህ ነው ወጥ ነው ልክ ነው መንገዱ
የተሳፈሩበት መርከቡ
ሊያናውጥ ቢጀምርም ወጀቡ
በመንገዱ የጠራው ታማኝ ነው
ከማዕበሉ መሀል የማይጥለው
ፀፀት የለበትም ፍፃሜው
ወትሮም ልክ ነበር ጅማሬው
መደምደሚያው ክብር ነው ሞገስ
ብድራቱን ጌታ ሲመልስ

ግጥምና ዜማ 1/09/2011 ተፃፈ
ኢየሩሳሌም ነጊያ
#ኢየሩሳሌም #የማያወላዳ
#ማቲ_7-13

#በጠበበው_ደጅ ግቡ፤ #ወደ_ጥፋት_የሚወስደው #ደጅ_ሰፊ፥ #መንገዱም_ትልቅ_ነውና፥ #ወደ_እርሱም_የሚገቡ_ብዙዎች_ናቸው፤