" ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፤"
(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6:6)
Music Arrangement &Guitar
Mihret Ab Berassa
mix Biruk Bedru
Chior Arrangement
Ermias Moll
#ገነቴ ነህ
የልባችንን ሀሳብ ፣የዐይናችን ትኩረት፣ የነፍሳችን ረሀብና የኑሮ ምኞታችንን ወደ ሰማይ ማየት ካላስለመድን፤ አንገቻችንን ወደ ምድር በማቀርቀር የህይወት አቋማችን ይጉብጣል፤ ሳቃችን የውሸት ሆኖ ደስታችን ይሰረቃል። ከእናታችን ማህፀን ከወጣንበት ጊዜ ጀምሮ እስከሽበታችን በዚህ ዓለም የኑሮ ዘይቤ ላይ ብቻ ከተንጠለጠልን አወይ ምስኪንነታችን፤ ጥቂቱን ቀዳዳ ደፈንን ብለን ስንፈነጥዝ የሚመጣው ቀዳዳ በእጥፍ ተቀዶ ሲጠብቀን ስንደፍን ሲቀደድ፣ አዲሱ ሲያረጅ ፣ ያረጀውን ስንጠግን፣ የጠገነውን ስንለውጥ ወዘት መቸም መኖር ደግ ይኸው ዛሬም አለን። በዚህ የፉክክርና የውድድር ዓለም ውስጥ ከማን አንሰህ(ሽ) ነው ለሚለን የምድር ቱልቱላ ለመስማት እህህ ብለን ጆሮአችንን ከመስጠት አልፈን ልባችንን ከስጠን አቤት ክስረታችን። " መዝገባችን ባለበት ልባችን ደግሞ በዚያ አለና።"(የሉቃስ ወንጌል 12:34)መዝገባችን ባለበት ደግሞ የህይወት ምዕራፋችን ይዘጋል። እንግዲ በክርስቶስ ከሆንን " ኑሮዬ ይበቃኛልን "(1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6:6) ልንማር ግድ ነው። ይህ ከሆነ ዘንዳ ኢየሱስ ክርስቶስ ያለምንም ማጀቢያና ማድመቂያ ድርብ ሸማችን ሆኖ በየትኛውም አቅጣጫ የሚመጣ የኑሮ ውርጭ ሳይጠብስን በእውነተኛ የክርስቶስ ደስታና እርካታ እንኖራለን። ኢየሩሳሌም ነጊያ
ባለብሰው ገላዬ አዲሱ ያረጃል
የተጫሙ እግሮቼ ሌላ ያምራቸዋል።
ደግሞ ይርበዋል ያበላሁት ሆዴ
ጥሜ ቆረጠ ስል ውሃ ጠማው አፌ።
የኑሮዬ ቋቱ ገደቡ ላይሞላ
ስባክን ስዳክር ብዬ እንዳልቀር ኃላ
ሰማዩን እረስቼ ምድሩን ቆንትጬ
አብላኝ አጠጣኝ ስል ለስጋዬ ሮጬ።
አይጠረቃ ህይወቴ አይሞላ ክፍተቴ
መቼ በቃኝ ያውቃል ይሄ ማንነቴ።
በምድራዊው አይደል በእህልና ውሃ
ለካስ እየሱስ ነው የመንፈስ ፍስሀ
ለካስ እየሱስ ነው የነፍሴ ፍስሀ።
የልቤ ሀሴት የውስጤ እርካታ
እየሱስ አንተ ነህ የነፍሴ ፋታ።
በአንተ ደስ ይለኛል ሁልጊዜ ሀሴት አደርጋለው
የሰጠኸኝ ደስታ ፍፁም ነው እፍለቀለቃለሁ
በአንተ ደስ ይለኛል ሁልጊዜ ሀሴት አደርጋለው
የሰጠኸኝ ተስፋ ፍፁም ነው እፈነድቃለሁ።
ባልበላም ጠግቤ አድራለው
ባልጠጣም እረክቼ እኖራለው
አንተ ካለህ ምን እሆናለው?
አንተ ካለህ ምን እሆናለው?
በረሀው ላይ አስቀኸኛል
ገነቴ ነህ አርክተኸኛል
ፍቅርህ ብቻ ይበቃኛል
መገኝትህ ያረካኛል
አንተ ካለህ ምን ያሻኛል
ፊትህ ብቻ ይበቃኛል።
Even if I wear new clothes, they will still get old.
Even if I put on new shoes, they will wear out too.
Even if I eat my fill from every plate, the hunger returns,
Even if I drink from every cup, the thirst comes back.
Oh, what could ever fill up my earthly vessel,
What could ever satisfy my body and soul,
If I should ever forget your kingdom?
Running for the earthly, or chasing after the worldly:
Why should I waste my days
Seeking after such things?
Life will not be filled; the absence will not depart.
The flesh will not do; the earth is not enough,
Bread will not satisfy, nor water quench
Oh, my soul’s rejoicing is in Jesus!
Oh, my spirit’s joy in Jesus!
My heart rejoices; my spirit abides,
Jesus: only you can slake my thirst!
Only you gladden my heart and lift high my spirit,
The joy that you have given me so overwhelms me:
That I think I shall laugh!
My heart rejoices, my spirit abides,
Jesus, in you is my soul’s content,
You gladden my heart, you lift up my soul.
The joy you have given me is so perfect
I am near to explode!
Even if I don’t eat – yet I am full;
Even if I don’t drink – yet I am satisfied;
Sine I have you, what else do I need?
Sine I have you, what else do I need?
You have made me laugh in deserts.
In you is both heaven and satisfaction.
Your love alone will suffice,
Only your presence will be enough,
Since I got you, what else do I need?
Even if I don’t eat – yet am I full;
Even if I don’t drink – still am I satisfied.
Since I have you, what else do I need?
Sine I got you, what else do I need?
You have made me laugh in deserts.
You are my heaven; in you I am satisfied.
Your love alone is enough for me,
Your presence alone is all I need.
Since I have you, what else do I need?
Your face alone is enough for me.
/ enegiya
#Genete_neh #You_are_my_heaven