በዚች ሕይወት ብቻ ክርስቶስን ተስፋ ያደረግን ከሆነ፥ ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን።"
if in this life only we have hope in Christ, we are of all men most miserable (1ኛ ቆሮ 15:19)
#ዓለም #Alem #2020
song written by Eyerusalem negiya
solo singers
Eyerusalem negiya
Ayda Abraham
Nahom markos
Lidia Anteneh
Ebba daniel
Biniyam yonas
Hiwot Tesfaneh
music&mix Robel Endal
Guitar Natinael desalegn
ግጥምና ዜማ ኢየሩሳሌም ነጊያ 13/5/07
ሙዚቃ ሚክስ ሮቤል እንዳለ
1-ዓለም ተሻሽላ ጸጥታ ሞልቶባት
ፍቅርና እምነት ፍትህ ሰፍኖባት
እውነት ተንሰራፍቶ ሆና የተወደደች
ለሰው ልጅ መኖሪያ ምቹ ትሆናለች።
እያሉ አንዳንዶች ተስፋ ያደርጋሉ
እንዲህ ነው ወይ እውነቱ ስናያት በቃሉ።
ወንድሙን ገዳይ የሌለው ፍቅር
ጌታን አይፈራ ሰውን አያፍር
ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላ ወዳዱ
ምቾት ፈላጊ ሲሆን ትውልዱ።
ነዋይ አፍቃሪ ገንዘብ አምላኩ
ገደብ አያውቅም አልፎ ከልኩ
እንዲናት ዓለም ይህች ናት ምድር
መቼ ሆነና የምንረግጠው አፈር።
ለእኔስ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል
ከሚመጣው ቁጣ ያድነኛል ይታደገኛል
ሳይመሽ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለናል
ከሚመጣው ጥፋትያድነናል ይታደገናል።
2-ሰጋ የለበሰ በክፋት አበደ
አንጀቱ ጨክኖ መሳዩን አረደ
ሰዶም አይን አውጣ ስር እየሰደደ
ሰው ከእንስሳ በታች ዘቅጦ ተዋረደ
በታላላቆች ጠብ ምስኪኑ ረገፈ
በዋዛ በከንቱ ህይወቱ ዓለፈ
ቀምቶ አዳሪ ያልዘራውን አጫጅ
የማይታመን ለወዳጅ የማይበጅ
ክብሩ በነውሩ ሆዱ አምላኩ
ለከት የሌለው አልፎ ከልኩ
ፅድቅን እረግጦ ኃጢያት የሚያስፋፋ
ውሸት አንግሶ እውነት የሚገፋ
የዓለምን ጥበብ በዘመን ለብሶ
እንዲያለ ትውልድ መጣ ገድግሶ።
አዝ
3 ተፈጥሮ እራሷ ፊቷን አዙራለሽች
ደመና ስትባል ሀሩር ትሆናለች
መልካም ዘር ተዘርቶ እሾ ታበቅላለች
ውላ እያደረች ጣህምዋን አትታለች።
አይ ምድር አሁንስ ታወቀብሽ
መደምደሚያሽ ጊዜው ፈጥኖ ደረሰብሽ
ማያጠግብ እንጀራ ከሩቅ ያስታውቃል
በዓለም ተስፋ የጣለ ሞኝ ሰው ይመስላል
እንግዲ እንንቃ እንዳንቀር ዋላ
የመጨረሻው ፅዋ ሲሞላ
እርኩም ሲረክስ ቅዱሱ ይቀደስ
ወደ እግዚአብሔር ፈጥኖ ይመለስ
ቀኒቱንና ጌዜውን ማን ያውቃል
የጌታ መምጫ እጅግ ተቃርቧል።
አዝ
4 ሰላምና እረፍት እርስ በእርስ መዋደድ
ወገን በወገኑ በዚያ ላይገደል
ሀዘንና ለቅሶ ዋይታና ሰቆቃ
በምድር ያለው ስቃይ ከቶ ሊያበቃ
መለከት በድንገት ሲሰማ
ጥሪው ሲያሰተጋባ የመለዐክቱ ዜማ
ሀሴት እርካታ ገንዘባችን ሆኖ
በደስታ ልንኖር እንባ ከዐይን ታብሶ
ጊዜያዊ ድንኳን ድንገት ሊፈርስ
ዘመን ሲፈጥን ስናይ ሲገሰግስ
ከሙሽራው ጋር ዘላለም ልንኖር
ፍፁማን ሆነን በስማዩ ክብር
አይቀርም ቶሎ እንሄዳለን
በመከኮት ሀይል ከፍ ከፍ ብለን።
አዝ ....